1/8የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል፡፡ በ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ሴት 1448 ወንድ 2158 በድምሩ 3606 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተምር ሲሆን ከዚህ ወስጥ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ ትምህርታቸውን ተምረው ያለፉ 378 ተማሪዎች እንደሚገኙበት ተጠቁሟል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ለመቀበል በርካታ የቅድመ ቅበላ ዝግጅት ያደረገ ሲሆን ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ ከባቡር ጣቢያ እና የአውቶብስ መናኽሪያ ጀምሮ አቀባበል በማደርግ እና ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን በማገዝ ላይ ይገኛል፡፡ የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የተማሪዎች ህብርት እና በየደረጃው ያሉ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችም ከዩኒቨርሲቲው ዋና መግቢያ ጀምሮ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
ዛሬ የተጀመረው የተማሪ ቅበላ እስከ ነገ እሁድ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ/ም የሚቀጥል ሲሆን ተማሪዎች የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 9 ቀን አጠቃላይ ገለፃ (Orientation) ተደርጎላቸው፣ ጥቅምት 10 ቀን ምዝገባ የሚያካሂዱ ይሆናል፡፡ ከጥቅምት 11 ጀምሮ የህይወት ክህሎት ስልጠና እና የመማር ማስተማር ስራ የሚጀመር መሆኑን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ፅ/ቤት አመልክቷል፡፡
ድሬዳዋ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት








